Welcome to
The Protect Ethiopia Children Coalition (PACC) webpage is hosted on the StopCSE.org website.

የኢትዮጵያን ልጆች ለመጠበቅ የሚደረግ የፊርማ ማሰባሰብ!

እኛ ከታች የፈረምን ወላጆች ፣ አያቶች ፣ አስተማሪዎች ፣ ሐኪሞች ፣ በሌሎች ልዩ ልዩ ሞያዎች የተሰማራን ፕሮፌሽናሎች ፣ አማካሪዎች ፣ ነጋዴዎች ፣ የሃይማኖት እና የህብረተሰብ መሪዎች ከ”የኢትዮጵያን ልጆች እንታደግ ጥምረት” ወይንም “Protect Children Ethiopia Coalition” ጋር በመተባበር ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት Comprehensive Sexuality Education (CSE)) በመባል የሚታወቀውን የትምህርት ዓይነት በኢትዮጵያ ሥርዓተ
ትምህርት ውስጥ ተካትቶ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ ሊደረግ መታቀዱን በሚቀጥሉት ሰባት ምክንያቶች አጠንክረን እንቃወማለን ፡፡

Read More

1. ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ከኢትዮጵያ ባህላዊ እሴቶች ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ ነው። ኤች አይ ቪን እና በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ታዳጊ ሴቶችን ርግዝና መከላከልን በማመካኘት የኢትዮጵያን የጾታ እና የወሲብ ሥነ-ምግባርን ለመለወጥ የሚፈልግ አደገኛ የሆነ በምዕራባዊያን መንግስታትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመራ አጀንዳ ነው ፡፡ በርካታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች በ”International Technical Guidance on Sexuality” በሚለው እኤአ የ2018 ህትመታቸው ላይ “በመብቶች ላይ የተመሠረተ” ብለው የሚያቀነቅኑትንና ጎጂ የሆነውን አጥፊ የወሲብ አጀንዳቸውን በግልፅ አሳይተዋል ፡፡ ይኸውም በሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በጭራሽ የግብረ ሥጋ
ግንኙነት እንዳይፈጽሙ ከማስተማር ይልቅ አንድ ልጅ “መቼ እና ከማን ጋር” ወሲብ ማድረግ እንዳለበት መወሰን ይችላል የሚለውን ፅንሰሀሳብ እንደሚያራምድ በህትመቱ ላይ አሳይተዋል ፡፡ በተጨማሪም ጎጂ የሆነ የጾታዊ ማንነት ርዕዮተ ዓለምን ፣ ወሲባዊ ሴሰኝነትን እና ውርጃን ያበረታታል ፡፡ ልጆች ከወላጆቻቸው የተለዩ ወሲባዊ እሴቶች እንዲኖVቸው እና በጾታዊ ግንኙነት ረገድ ማህበራዊ ተቀባይነት ያላቸውን ደንቦችና እሴቶች ጥያቄ ውስጥ እንዲያስገቡ ይጠይቃል ፡፡

2. ያለወላጅ ተሳትፎ ፣ መመሪያ እና ፈቃድ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ካሪኩለምን ማውጣት በዓለም አቀፍ ህግ የተቀመጡ የወላጆች መብቶችን ይጥሳል። ኢትዮጵያ ፈራሚ የሆነችባቸው በርካታ ወሳኝ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች እንደሚደነግጉት ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ይዘት የመወሰንና የመምራት “ቀዳሚ መብት” አላቸው ፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ወላጆች በሥርዓተ ትምህርታችን ውሥጥ እንዲካተት ግፊት እየተደረገበት ያለውን ወሲብ ነክ ሥርዓተ ትምህርትን የማየትና የመገምገም ዕድል አልተሰጣቸውም፡፡

3. UNFPA የተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲ ፣ ከሌሎች የተባበሩት መንግስታት
ኤጄንሲዎች እና የውጭ መንግስታት ጋራ በመተባበር በኢትዮጵያ እና በተቀሩት የአፍሪካ ሐገራት ውስጥ
ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE)ን የመተግበር አጀንዳ እየመሩ ይገኛሉ ፡፡ ለምሳሌ UNFPA በስዊድን

መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ በተዘጋጀውና እና “Basic and Higher Institutions of Learning in KwaZulu-Natal” በተሰኘውና ደቡብ አፍሪካን አስመልክቶ ባዘጋጁት ህትመታቸው (ለመመልከት https://southafrica.unfpa.org/sites/default/files/pub-pdf/UNFPA_CSE_report_web.pdf) በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ተፈጻሚ እንዲሆንይጠይቃል። በተጨማሪም እጅግ አወዛጋቢ ለሆኑት ጉዳዮች ማለትም ለወሲባዊ ዝንባሌ (sexual orientation) ፣ ለጾታዊ ማንነት (gender identity) ፣ የወሲባዊ ስሜት አገላለጥ ልዩነት (sexual diversity) እና ለሁሉም የወሲብ ምርጫዎች (sexual preference) አክብሮት የመስጠትን ጉዳይ ትኩረት እንዲሠጠው ይጠይቃል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኩል ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በጭራሽ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዳይፈጽሙ ከማስተማር ይልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ግብዣን አልፈልግም ብሎ የመመለስ መብት እንዳላቸው በዚሁ በሁሉን አቀፍ ጾታዊ ትምህርት (CSE) አማካኝነት ያስተምራል፡፡
በወሲባዊ ተግባር የሚሳተፉ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ያሉ ልጆች ብዙውን ጊዜ የሚከተሉት አሉታዊ ውጤቶች ያጋጥሟቸዋል።

  • የርግዝና መከላከያ የመጠቀም ዕድላቸው አነስተኛ ነው፤
  • በተላላፊ የአባለዘር በሽታዎች የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፤
  • የአሁን ወይንም የህይወት ዘመን የወሲብ ጓደኛዎቻቸው በርካታ ይሆናሉ፤
  • የማርገዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፤
  • ትምህርት ማቋረጥ (ከእርግዝና ጋር ባይገናኝ እንኳን)፤
  • የወሲባዊ ጥቃት ሰለባነት መጨመር፤
  • ድብርትን (Depression) ጨምሮ አጠቃላይ የአካላዊ እና የሥነ-ልቦናዊ ጤና መቃወስ፤
  • መልካም እና የተረጋጋ ግንኙነት የመመሥረት እድላቸው ዝቅተኛ ሲሆን የመፋታት እድላቸው ደግሞ ከፍተኛ ነው፤
  • እንደ ማጨስ ፣ መጠጥና አደንዛዥ ዕጾች ባሉ ሌሎች የአደጋ ተጋላጭነቶች ላይ ከፍ ያለ ተሳትፎ፣
  • ከማህበራዊ ህይወት መራቅ ወይም በግለኝነት ባህሪ የመሳተፍ እድላቸው ሰፊ ነው፤
  • በራሳቸው ውጤታማ የመሆን እና ራስን የመቆጣጠር ዕድላቸው አነስተኛ ነው፤
  • ከወላጆች ፣ ከት/ቤት እና ከእምነት ጋር ቁርኝታቸው ይቀንሳል፤

4. በተባበሩት መንግስታት ኤጄንሲዎች እና በምዕራባዊ መንግስታት የሚደገፉትን ጨምሮ የሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) መርሃግብሮች ከወሲባዊ ጤና (sexual health) ይልቅ “ወሲባዊ መብቶች”
(sexual rights) ላይ ትኩረት በማድረግ ሞራላዊ የሆነ የወሲባዊ ትምህርት አቀራረብን ሳይሆን ፣ አወዛጋቢውንና በ“መብቶች ላይ የተመሠረተ” አካሄድን ይከተላሉ፡፡

5. ኢትዮጵያ አወዛጋቢውን “Ministerial Commitment on Comprehensive Sexuality Education and Sexual and Reproductive Health and Rights for Adolescents and Young People on Eastern and Southern Africa (ESA)” የሚባለውን ሰነድ ስትፈርም ከሚመለከታቸው የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ከሁሉም በላይ ደግሞ ልጆችን የማሳደግ ቀዳሚ ኀላፊነትና አደራ ካለባቸው ከወላጆች ጋራ አስፈላጊ የሆነ ምክክር አለማድረÒ ወላጆች የልጆቻቸውን ትምህርት እንዲመሩ የተሰጣቸውን መብት ወደጎን ያደረገ ነው።

6. “National Adolescent Sexual and Reproductive Health and Rights (ASRHR) Framework Strategy” የተባለውም ሰነድ እንዲሁ ለምምክር ያልተጠሩ ወላጆችን መብቶቻቸውን የጣሰ ሲሆን
የተባበሩት መንግስታትንና እና የምዕራባዊያንን ከወሲባዊ ጤና (sexual health) ይልቅ “ወሲባዊ መብቶች” (sexual rights) ላይ ያዘነበለውን አቋማቸውን የሚያንፀባርቅ ነው። በዓለም ዙሪያም በተባበሩት መንግስታት ወኪሎች የወላጆችን መብት የጣሱ ተመሳሳይ ስትራቴጂዎች ወደፊት እየተገፉ ናቸው ፡፡

7. ከሁሉም በላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ውጤታማ እንደሆነ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ልጆችን እርግዝና እና HIVን ጨምሮ
በግብረሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን እንደሚከላከል እንዲሁም መታቀብ ደግሞ በተቃራኒው ውጤታማ እንዳልሆነ ያስረዳል ሲሉለት የነበረው “ጥናት” በቅርቡ በአንድ ሌላ ዓለም አቀፍ በሆነ ጥናት
ፈጽሞ ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተረጋግጧል። በSexEdReport.org ላይ ሪፖርት በተደረገው አዲስ ዓለም አቀፍ ትንታኔ መሠረት ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) በከፍተኛ ሁኔታ
ማለትም በ87 ፐርሰንት ያህል የወደቀው ወይንም ውጤት አልባ የሆነው በአፍሪካ ውስጥ እንደሆነ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ (24%) ያስከተለውም አፍሪካ ውስጥ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ይህንን “Re-Examining the Evidence for Comprehensive Sex Education in Schools – A Global Research Review,” በሚል ርዕስ የወጣው ጥናት ውስጥ የተካፈሉት ተመራማሪዎች በUNESCO እንደ አስረጂ የተጠቀሰውን ምርምር ተመልክተው የሚከተለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።

“በሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ በተደረጉ ምርምሮችና ጥናቶች መሠረት ት/ቤቶችን ያማከለ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት(CSE) ውጤታማ የህዝብ ጤና አጠባበቅ ስትራቴጂ መሆን እንደማይችል ተረጋግጧል፤ በአሜሪካ እና ከአሜሪካ ውጭ ከመከላከል ጋራ በተያያዘ በጣም ውሱን የሆኑ ዘላቂ ውጤቶችን ብቻ አስገኝቷል ፡፡ በእርግጥም ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት ማለትም CSE ከስኬት ይልቅ እጅግ የላቀ
ውጤት አልባነትን(failure) አሳይቷል፤ በርካታ ጉዳቶችንም ማስከተሉም ተረጋግጧል…
አጥኝዎቹ በስተመጨረሻ የሚከተለውን ብርቱ ማሳሰቢያ እንደሚከተለው አስተላልፈዋል፣
”በግብረሥጋ ግንኙነት ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችና እርግዝና በዓለም ዙሪያ ለወጣቶች ጤና እና ደህንነት ስጋት መሆናቸውን ስናይ ፤ ወደ 30 ከሚጠጉ ዓመታት በኋላና እና 103 ከሚሆኑ ተዓማኒነት ካላቸው ጥናቶች በኋላ የደረስንበት ድምዳሜ ትምህርት ቤቶችን ያማከለ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት ፈጽሞ ለውጤታማነቱ ምንም ዓይነት አስተማማኝ የሆነ ተጨባጭ መረጃ ባለመኖሩ ፖሊሲ አውጪዎች በዓለም ዙሪያ ሁሉን አቀፍ የጾታ ትምህርትን ለመተግበር ያወጧቸውን እቅዶች እርግፍ አድርገው በመተው በጉርምስና ዕድሜ ላይ በሚገኙ ልጆች ላይ የወሲባዊ ልምምዶች የሚያስከትሏቸውን መጥፎ ውጤቶችን ለመቀነስ ሌሎች አማራጭ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡ የመታቀብን አዎንታዊ ውጤቶችን በተመለከተም ተጨማሪ ጥናቶች መደረግ አለባቸው።”

ለማጠቃለል ያህል ውጤት አልባ መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ የተረጋገጠውንና እና ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለውን ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን (CSE) በት/ቤቶቻችን ውስጥ ለማቅረብ ምንም ዓይነት ህጋዊ ግዴታ የለብንም ፤ ከህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ አንጻርም ሁሉን አቀፍ የጾታ ትምህርት (CSE) ጠቃሚ ውጤት ስለማምጣቱ የተጨበጠ ማስረጃም የለም። ከነዚህ ሁሉ አስደንጋጭ እውነታዎች አንፃር እኛ ፊርማችንን ከዚህ በታች ያሰፈርን ዜጎች የኢትዮጵያ መንግስት እና በተለይም የትምህርት እና የጤና ሚኒስትሮቻችን የሚከተሉትን ሰባት እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲወስዱ በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡

1. ኢትዮጵያ ሐገራችን ከሌሎች የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሐገራት ጋራ የሁሉን አቀፍ የጾታ ትምህርትን (CSE) ተግባራዊ ለማድረግ ከፈረመችው ስምምነት (Eastern Southern Africa Commitment on
CSE) በፍጥነት እንድትወጣ (የCSEን አጀንዳ ሳይረዱ የፈረሙ በርካታ የአፍሪካ አገራት አሁን ለመልቀቅ እየሰሩ ናቸው፡፡)
2. አወዛጋቢ የሆነውን የብሔራዊ የጎልማሶች ወሲባዊ እና የተዋልዶ ጤና እና መብቶች ማዕቀፍ ስትራቴጂን (National Adolescent Sexual and Reproductive Health and Rights (ASRHR) Framework Strategy) ተግባራዊ ከማድረግ እንድንቆጠብ
3. በሙሉም ሆነ በከፊል የሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን (CSE) ሐሳብ የያዙ የተጀመሩም ሆነ በዕቅድ ላይ ያሉ ፕሮግራሞች ሁሉ እንዲወገዱ ( ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) የሚያካትታቸውን 15 ጎጂ ሐሳቦች በhttps://www.comprehensivesexualityepted.org/wp-content/uploads/Harmful-Effects-10.17.17.pdf ላይ በመሄድ ይመልከቱ)
4. ወላጆች እና አሳዳጊዎች የልጆቻቸውን የጾታ ትምህርት በመምራት ፣ በመቅረጽ እና በመቆጣጠር ረገድ ያሏቸው መብቶች እውቅና እንዲሰጣቸውና እንዲከበሩ
5. በኢትዮጵያ ውስጥ ከእንግዲህ ማንኛውንም ዓይነት የሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (CSE) ይዘቱ እየተቀየረ በተለያየ መልክ ወደ ሥርዓተ ትምህርታችን በማንኛውም መልክ እንዳይካተት
6. ከማንኛውም ዓይነት የወሲብ ባህሪ መታቀብን (በወሲብ ድርጊት ተሳታፊ የሆኑትን ወጣቶችን ደግሞ ወደመታቀብ እንዲመለሱ ማድረግን) በሁሉም የወሲብ ሥርዓተ-ትምህርት እና መርሃግብሮች ውስጥ
በዋናነት አቋም ተደርጎ እንዲደገፍ
7. የትኛውም የኢትዮጵያ የሕዝብም ሆነ የግል ትምህርት ቤት በየትኛውም የትምህርት መመሪያው ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዮችን ማካተት እንደማይችል ማረጋገጥ፡-

ሀ. በልጆች መካከል የሚደረግ ወሲባዊ ተግባርን ኖርማል እንደሆነ ማስተማር ወይም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በወሲባዊ ተግባር ውስጥ ሲሳተፉ የሚያሳይ ወይም የሚገልጽ ምሳሌዎችን መጠቀም
ለ. ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች መካከል የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ወሲባዊ ተግባር ከጠንቅ የፀዳ ወይም አደጋ የሌለው ሊሆን እንደሚችል መጠቆም
ሐ. ስለ ግለወሲብ (Masturbation) ወይም በአፍ ወይም በፊንጢጣ ስለሚደረጉ ወሲባዊ ግንኙነቶች የሚገልጹ ቁሳቁሶችን ወይም ይዘቶችን በትምህርት ውስጥ ማካተት
መ. ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችላቸውን መንገዶች ከማሳየት ባለፈ ወሲባዊ መብቶች እንዳሏቸው የሚያመለክቱ ሐሳቦችን ማንጸባረቅ
ሠ. የሚከተሉትን አሉታዊ የሆኑ የጾታዊ ማንነት (gender Identity) ፅንሰ-ሀሳቦች፣ ቁሳቁሶችን ወይም ይዘቶችን ማካተት

i. ጾታ ሊለወጥ የሚችል ነው፤
ii. ጾታ ቋሚ አይደለም፤
iii. ጾታ በተፈጥሮ ሳይሆን በራስ የሚወሰን ነው፤
iv. ከወንድ እና ከሴት ውጪ ሌሎች ጾታዎች አሉ፤
v. የወንዶች እና የሴቶችን ተውላጠ ስሞች በመቀያየር እንዲጠቀሙ ማበረታታት
vi. ልጆች በወሲባዊ ምርጫቸው (sexual preference) መሠረት እንዲለዩ ማበረታታትን
የመሣሠሉ አመለካከቶችን ማራመድ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌላቸው እንዲታወቅ እንሻለን፡፡

ከጾታ ማንነታቸው ጋር ለሚታገሉ ልጆች ርህራሄ እና ድጋፍ ሁል ጊዜም መሰጠት እንዳለበት በጽኑ እናምናለን ፣ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ርህራሄ ሕፃናትን ከእውነታው ተቃራኒ ወደሆነ ማንነት እና ለህይወት ዘመን መካንነት ወደሚዳርጋቸው የህክምና ጣልቃ ገብነት እና ቀዶህክምና በማምራት በሐሰት እምነት አስሮ ሊቆልፍባቸው አይገባም። ስለሆነም ቀደም ሲል የተጠቀሱትን እርምጃዎች በመውሰድ የኢትዮጵያን ልጆች ለመጠበቅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡

የሀገራችን የወደፊት ዕጣና የልጆቻችን የወደፊት ሕይወት አደጋ ላይ ነው!

ከሠላምታ ጋር ፣

 

ፊርማዎትን
https://www.comprehensivesexualityeducation.org/international-map/ethiopia/ ላይ በመሄድ ያስፍሩ

 

የኢሜይል አደራሻ (ፊርማዎን ይወክላል)
ስም
የአባት ስም
የስልክ ቁጥር

ፊርማዎን ያስገቡ(Submit)

Click Here to Read Petition in English

Protect Ethiopia Children Petition!

We, the undersigned parents, grandparents, teachers, doctors, counselors, business, religious, and community leaders, in association with the Protect Children Ethiopia Coalition, strongly oppose the proposed implementation of Comprehensive Sexuality Education (CSE) in the curriculum in Ethiopia’s public schools for the following seven reasons:

1. CSE runs counter to Ethiopia’s cultural values. CSE is a harmful Western- and UN-driven agenda that seeks to change Ethiopia’s gender and sexual norms under the guise of HIV and teen pregnancy prevention. Multiple UN agencies clearly revealed their harmful “rights-based” sex agenda in their 2018 publication, “International Technical Guidance on Sexuality.” This publication reveals that CSE promotes “the right to decide when and with whom” a child will have sex rather than discouraging children of minor age from engaging in sex at all. It also promotes harmful gender identity ideology, sexual promiscuity and abortion. It recommends asking children to “differentiate” their sexual values from their parents and to “question” social norms on sexuality.
2. Rolling out CSE without prior parental involvement, guidance and approval violates well-established parental rights. According to multiple binding and nonbinding international human rights documents that Ethiopia is a party to, parents have the “prior right” to guide the education of their children, and yet parents have had no opportunity to view, evaluate and approve of any proposed sexuality curriculum.
3. UNFPA , among other UN agencies and foreign governments are driving the CSE agenda in Ethiopia and the rest of Africa. For example, UNFPA, in their publication funded by the Swedish government titled, “Basic and Higher Institutions of Learning in KwaZulu-Natal,” (see at https://southafrica.unfpa.org/sites/default/files/pub-pdf/UNFPA_CSE_report_web.pdf) calls for a “roll out and implementation of CSE nationally” and discusses the controversial issues of “sexual orientation,” “gender identity,” and “sexual diversity” and respect for “all sexual preferences.” It also reveals, that through CSE “children will also be taught that you have the right to say no to sex” rather than, again, discouraging children of minor age from engaging in sex at all. Yet teens who are sexually active often experience many of the following negative consequences:
• Less likely to use contraception
• More likely to experience an STI
• More concurrent or lifetime sexual partners
• More likely to experience pregnancy
• Lower educational attainment (not necessarily linked to pregnancy)
• Increased sexual abuse and victimization
• Decreased general physical and psychological health, including depression
• Decreased relationship quality, stability and more likely to divorce
• More frequent engagement in other risk behaviors such as smoking, drinking and drugs
• More likely to participate in antisocial or delinquent behavior
• Less likely to exercise self-efficacy and self-regulation
• Less attachment to parents, school and faith
4. CSE programs, including those promoted by UN agencies and western governments , take a controversial “rights-based” rather than health-based approach to sex education emphasizing “sexual rights” over sexual health.
5. Ethiopia’s signing on to the “Ministerial Commitment on Comprehensive Sexuality Education and Sexual and Reproductive Health and Rights for Adolescents and Young People on Eastern and Southern Africa (ESA)” was done without proper consultation with the appropriate branches of government and without proper regard for the rights of parents to direct their children’s education.
6. The “National Adolescent Sexual and Reproductive Health and Rights (ASRHR) Framework Strategy” also violates the rights of parents who were not consulted and reflects a UN and Western governmental sexual rights rather than sexual health approach. Similar “framework” strategies are being pushed by UN agencies all across the globe in violation of parental rights.
7. Most importantly, the research UN agencies use to claim CSE is effective and will prevent teen pregnancy and STDs including HIV and that abstinence education is ineffective has recently been thoroughly discredited in a global study. According to this new global analysis found at SexEdReport.org, CSE has the highest failure rate in Africa (89% failure rate) and the highest rate of negative impacts (24%) in Africa as well. The researchers in this study titled, “Re-Examining the Evidence for Comprehensive Sex Education in Schools – A Global Research Review,” looked at the research referenced by UNESCO and concluded: “Three decades of research indicate that school-based comprehensive sex education has not been an effective public health strategy—it has produced only a few sustained effects on protective out- comes, without other negative impacts, in U.S. and non- U.S. settings combined. In fact, it [CSE] has shown far more evidence of failure than success and caused a concerning number of harmful effects … Given the threat posed by STDs, HIV, and pregnancy to the health and well-being of young people worldwide, and the compelling lack of evidence of effectiveness for school-based Comprehensive Sex Education after nearly 30 years and 103 credible studies, we recommend that policymakers abandon plans for its global dissemination and pursue alternative prevention strategies for reducing the negative consequences of adolescent sexual activity. Further studies of the positive findings for abstinence education should be done to inform the development of such paradigms.”
In conclusion, there is neither a legal obligation to provide failed and highly controversial
CSE in our schools, nor evidence to support CSE from a health perspective. In light of all of these alarming facts, we, the undersigned, respectfully request the Ethiopian government, and in particular our Ministers of Education and Health, to urgently take the following seven actions:
1. Withdraw from the Eastern Southern Africa Commitment on CSE. (Several other African countries that did not understand the CSE agenda when they signed it are also now working toward withdrawing.
2. Abandon the controversial “National Adolescent Sexual and Reproductive Health and Rights (ASRHR) Framework Strategy.”
3. Withdraw all ongoing or intended programs containing any and all elements of CSE. (See 15 common harmful CSE elements at https://www.comprehensivesexualityeducation.org/wp-content/uploads/Harmful-
Effects-10.17.17.pdf)
4. Recognize and respect the rights of parents and guardians in guiding, shaping and influencing the education and especially the sex education of their children.5. Ban the reintroduction of any and all harmful elements of CSE in its various formats from any curricula or programs in Ethiopia.
6. Mainstream the promotion of abstinence (or a return to abstinence for sexually active youth) from all sexual behavior as the expected standard for all Ghanaian children of minor age, throughout all sex education curricula.
7. Ensure that no Ethiopian public school shall include in any of its courses of study instruction which:
a. Normalizes sexual conduct between minors or uses examples depicting or describing children of minor age engaged in sexual conduct.
b. Suggests that any type of sexual conduct between minors can be safe or without risk.
c. Includes materials or content about masturbation or oral or anal sexual contact.
d. Includes materials or content that suggests that children of minor age have sexual rights beyond those related to protection from abuse.
e. Includes materials or content about gender identity theory including the following concepts:
 that gender or sex can be fluid or changeable
 that gender or sex exists on a spectrum
 that gender or sex is self-determined rather than biologically determined
 that genders or sexes exist other than male or female
 that teaches children to use female pronouns for males and vice versa
f. Encourages children to identify according to their sexual preferences.
We affirm that compassion and assistance should always be given to children struggling with their gender identity, but such compassion should not consist in affirming children in an identity that is counter to reality and that can lock them into a false belief leading to medical interventions and mutilating surgeries that leave children infertile for life. We, therefore, respectfully request that you give this matter your most urgent attention and immediately act to protect Ethiopian children by taking the aforementioned steps. The future of our nation—and our children—is at stake.
Sincerely,

[Your Email Signature]

Sign the Petition

30,000
22,699 
22,699 people have signed. Help us reach 30,000 signatures.
  • Your email counts as your signature and will be kept private.
  • Hidden

Join the Coalition as an Individual

  • Please enter your Contact Information:
  • Hidden

Join the Coalition as an Organization

  • Organization Information:
  • Organization Contact Information:
  • Hidden

RESOURCES

View Our Mission & Objectives

Mission:

To protect the health and innocence of children and the fundamental rights of parents to direct the education, healthcare and upbringing of their children.

Objectives:

  • To advocate for laws and policies that will protect children and parental rights.

  • To expose the harmful nature of comprehensive sexuality education (CSE), gender ideology, and pornographic materials and prevent any such materials, programs or ideologies from being distributed, implemented or promoted in schools.

  • To inform and mobilize concerned citizens including parents, grandparents, teachers, young people, policymakers, government officials, and business, religious and community leaders to protect our children.

Watch the Videos:

Harmful UN-Supported CSE:
Regional Module for Teacher Training on Comprehensive Sexuality Education for East and Southern Africa International Technical Guidance on Sexuality Education  (2018 UNESCO, UNFPA, UNICEF, UNAIDS, UN WOMEN, WHO) Fulfil! Guidance document for the implementation of young people’s sexual rights   (World Health Organization, UNESCO) International Guidelines on Sexuality Education (2009 UNESCO) Standards for Sexuality Education for Europe  (World Health Organization)

View our Upcoming Meetings

  • Coming Soon!

This website was created to warn parents and policy makers of the serious harms of explicit comprehensive sexuality education programs.

This project is a joint effort of “Family Policy Institute, Ethiopia”,  Family Watch International, UN Family Rights Caucus.